ethiopiantimes

May 17, 2011

የይድረሱልን ጥሪ

Filed under: Ethiopia — ethiopiantimes @ 2:21 pm
Tags: , , , , ,

የይድረሱልን ጥሪ
ብቃት ያለዉ አመራር የአንድን ሥራ መሠረታዊ ምንነት፣ለምን እንደሚሠራን እንዴትስ ብሠራ ዉጤታማ እንደሚሆን ግንዛቤ የለዉ ነዉ፡፡ የሥራዉ ምንነት በመደበኛ ትምህርት፣ መጽሐፊትንና የተለያዩ ጽሁፎችን በማንበብ የሚገኝ ሲሆን ሥራዉ ለምን እንደምሠራ ለማወቅ ደግሞ የመስሪያ ቤቱንና ባጠቃላይ ሀገራዊና ህዝባዊ ራዕይን በመገንዘብ ነዉ፡፡ እንዴት እንደሚሠራ ሙያዊና ተክንካዊ ብቃትን ለመካን ከስልጠና ባለፈ በተጨባጭ ሥራዉ ዉስጥ በተግባር በመፈተሽ የሚዳብር ይሁናል፡፡
አነሳሴ በአመራር ሳይንስ ላይ ትንተና ለማቅረብ ሳይሆን የከተሞች ልማትና መልካም አስተዳደር ዉስብስብና አስቸጋሪ መሆኑ በተደጋጋሚ ይነሳል፡፡ የሱሉልታ ከተማ ችግር ደግሞ ከየትኛዉም የባሰበት ሆኖ የገኛል፡፡ ባድሱ ምዕተ ዓመት መባቻ የከተማየቱን የመጠጥ ዉኃ ችግር እንዳይነሳ ላማድረግ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸዉን በወቅቱ የነበሩት የከተማዉ ካንትባ በህዝቡ ፊት ቃል መግባታቸዉ የታወሳል፡፡ በ1999/2000 መሆኑ ነዉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በ2002 የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤት ምርጫ ወቅት ለሚቀጥሉት ዓመታት ሀገራችንን የማስተዳደርና ልማቷን ለመምራት ዕድሉ ያገኘን እንደሆነ ዳግም የመጠጥ ዉኃ ችግር አይነሳም በማለት ህዘቡን ቀስቀሰዉበታል፡፡ በአድስ አበባ ከተማ ካለዉ የመኖሪያ ችግር ለማምለጥ ብዙ ሰዎች፣ ያሉትን የመሠረተ ልማት ችግር ይፈታሉ የሚል ተስፋ ሰንቀዉ መሬት በመወሰድም ሆነ በመግዛት የገነቧቸዉ የመኖሪያ ቤታቸዉ በዚሁ የመጠጥ ዉኃ ችግር ምክንያት ሳይገቡባቸዉ በመቆየታቸዉ የሌቦች ከለላ ከመሆናቸዉ ባሻገር እያረጁና እየወደቁም ይገኛሉ፡፡
የሱሉልታ ከተማ መስተዳድር የዉስጥ ለዉስጥ መንገድ፣ ባህላዊ ሀዉልትና አደራሽ ፕሮጄክቶችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ የእንደነዚህ ዓይነቶቹ ፕሮጄክቶች ከህዝቡ የዕለት ተለት ሕይወት ጋር በቀጥታ ባይያያዝም መሠረታቸዉ ምንም ክፋት የለዉም፤ በቂ በጄት እስካለ ድረስ፡፡ የህዝቡ ወቅታዊና ቀጥተኛ ጥያቄ ግን ባህላዊ ሀዉልትና አደራሽ ልሆን አይችልም፡፡
መንገድ መስራት ለትራንስፖርት ከሚሰጠዉ አገልግሎት በተጨማሪ የሥራ ዕድል በመፍጠርና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በማፋጠን ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ፡፡ ይሁን እንጅ እየተሰራ ያለዉ መንገድ በተለያዪ ችግሮች የተሞላ ነዉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ከመንገዱ ጋር መሠራት የሚገባቸዉ የተፋሰስ ቦዮች ታስቦበት አልተሰራለትም፡፡ በሌላ በኩል እየተሠሩ ያሉ መንገዶች ነዋሪዎች በብዛት ከገቡባቸዉ ሠፈር ይልቅ አዳድስ የተመሩና መሀንድሶችና ደላላዎቻቸዉ ልቸበችቧቸዉ ያዘገጇቸዉ አካባቢዎች ዋጋ እንድያወጣላቸዉ ይሁን ተብለዉ የተሠሩ መሆናቸዉ ለከፍተኛ ወጪ እንጅ ለአገልግሎት እንዳለታሰቡ የአካባኒዉ ህብረተሰብ አጃእብ ነዉ ከማለት ዉጪ ምንም ልጨምርበት አልቻለም፡፡ ከዚህም በላይ መንገዶቹ የተበጣጠሱና ከዋናዉ መንገድ ጋር ያልተገናኙና የህብረተሰቡን ችግር ለመፈታት ታልሞ የተሠሩ ያለመሆናቸዉ ነዉ፡፡ ይህም ብሆን ሌላ ተጨማሪ ገቢ የስገኛቸዋል፡፡ ጨርሱልን ብባሉ የአካባቢዉ ህዝብ በልማት ኮምቴዉ በኩል በማስተባበር መዋጮ እንድሰበስቡ በግልጽ በማዘዝ ባስቀመጡት የታርፍ መስፈረት ተሟልቶ ስገኝ ይሠሩላቸዋል፡፡
እነዚህ መሀነድሶች መጀመሪያ ከመደበኛዉ የገቢ ምንጫቸዉ ከመሬት አስተዳደርና አሰጣጥ ተነስተዉ ወደዚህኛዉ መሠረተ ልማት ስዛወሩ፣ ላለመነሳት አልቀሰዉና አማላጅ ልከዉ ያልመከሩት ዘዴ አልነበረም፡፡ ሳይነሱ ከዚሁ መሬት ጋር ከተያያዘ ሥራ ላይ የቀሩት ለአመራሩ ምስጋናና የተለያዩ ገጸበረከቶችን ስያበረክቱ ሰንብተዉ ነበር፡፡ ምክንያቱም በአቋሯጭ ሚልዬነር የመሆን ጉዳይ ነዉና፡፡
እያደር ግን ከካርታና መሬት ጋር ላይ ታች ከማለት በቀጥታ ከመንግስት ካዝናና ከህዝቡ መዋጮ ጥሬ ገንዘብ ማጋበሱ የበለጠ ቀላል ዘዴ እንደለለም አረጋገጡ፡፡ ለዚህም ወቅታዊ ዘዴያቸዉ በተለያዩ ሥፍራዎች የዉኃ፣ የመንገድና ሌሎች የልማት ፕሮጄክቶችን ጀምረዉ ባጄት አጣን፣ ገነዘብ ጨርሰናል የሚሉ ሰበቦች ማቆምና ህዝቡ መዋጮ እንድያሰባስብ ማስገደድ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
አንድ ፕሮጄክት ተጠንቶ ስቀርብ ከቅደመ ዝግጅት አንዱና ዋነኛዉ የባጄት ምንጩን ማፈላለግና አጠቃቀሙን መቅረጽ እንደሆነ በተለያዬ ጊዜ የሰማሁ ይመስለኛል፡፡ ብዙ ፕሮጄክቶችን ጀምረዉ ማቆም ምረጥ ተሞክሮ ነዉ ተብሎ ይሁን?
እዉነት ለልማቱ ድጋፍ የሚሆን ገንዘብ ፈልገዉ ከሆነ የተለያዬ ኢንቨስትመንት መሬቶችን ክራይና ሊዝ ክፍያ ብቻ በጥንቃቄ ብፈትሹና ለማሰባሰብ ብፈልጉ መረጃዉ በእጃቸዉ ነዉ፡፡ እራሳቸዉ በየዕለቱ የምጠቀሙባቸዉ የጓደኞቻቸዉና የዘመዶቻቸዉ የንግድ ድርጅቶችም ብሆኑ ዓይናቸዉ እያዬ የመንግስትን ገቢ በሕገወጥ መንገድ ስሰበስቡ አይቶ እንዳላየ እያለፉ ነዉ፡፡ ፍትሐዊ ገቢን በብቃት ለመሰብሰብ ብፈልጉ ኖሮ የሚያግዛቸዉና የሚደግፋቸዉ የመንግስት መዋቅር ከጎናቸዉ ጠፍቶ ነዉ? እራሳቸዉ ስላልፈለጉት ነዉ እንጅ፡፡
ለማጠቃለል፤ እነዚህ የኛ አመራሮች በያመቱ ችግሮችን አንፈታለን ብሎ ቃል ከመግባት በተግባር መስራቱ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነታቸዉን እነደምያረጋግጥላቸዉ ጠፍቷቸዉ ይሁን፣ ወይስ የተሻለዉን መምረጣቸዉ ነዉ? ምን ዓይነቱ መሠረተ ልማት ለምን፣ የትና እንዴት ተቅዶ ልሠራ ይገባል ብሎ ራሳቸዉን መጠዬቅ ተስኗቸዉ ነዉ ወይስ የሚያዋጣቸዉን መርጠዉ ነዉ?
በዚህ ሥራ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋሪ ድርሻ ያላችሁ ሁሉ ለሕልናችሁ ተገዥ ካልሆናችሁ ዞሮ ዞሮ ከሀገር እንኳን ብታመልጡ ከህልናችሁ ጸጸት የማታመልጡ መሆናችሁን እንድትገነዘቡ፡፡ በዚህ ምድራዊ ሕግ ፍርድ ባታገኙም እንኳን በታርክ ተወቃሽ ከመሆን አትድኑም፡፡ ልጆቻችሁ ይህን ታሪክ በሰሙና ባነበቡ ቁጥር የረግሟቸዋል፣ሀገራቸዉንና እራሳቸዉንም ይጠላሉ፡፡ በየትኛዉም ኃይማኖት መዋሸት፣ መስረቅ፣ የሌላን ሰዉ ሀብት መዘረፍም ሆነ መብት መጣስ አይፈቀድም፡፡ ያስጠይቃል፡፡
ሕብረተሰባችንም ይህን ጥቃት ሰምቶ እንዳልሰማ፣ አይቶ እንዳላዬ ከመሆን ነቅቶ በመከታተል አስፈላግዉን የመደብ ትግል እንድያደርጉ ጥሪዬን እያስተላለፈኩ የሚመለከተዉ አካልና ይህን ጽሁፍ አንብባችሁ የተረዳችሁ ሁሉ አስፈላጊዉን ትብብር እነድታደርጉልን በህዝባችን ስም አማፀናችሀለሁ፡፡
ወጣት ለሚ ቀበታ
ከሱሉልታ

Advertisements

Create a free website or blog at WordPress.com.